top of page

አቢጋኤል ዮሐንስ ፋውንዴሽን

​

አቢጋኤል ለመጻሕፍት ልዩ ፍቅር የነበራት ወጣት ነበረች። መጻሕፍትን ብቻ አታነብም ነበር፤ በውስጣቸው ያሉ ታሪኮችን፣ ስሜቶችን እና ሀሳቦችን በጥልቀት ትረዳ ነበር።

​

መጻሕፍት የተለያዩ ሰዎችን ታሪክ እንደታውቅ፣ ባህሎችን እና የሕይወት ተሞክሮዎችን እንድትረዳ ይረዷት ነበር። እንደ ጥሩ የመጽሐፍ ገምጋሚ፣ ያነበበችውን መጽሐፍ ሀሳብ፣ እና የተረዳችውን ቁምነገር  ለሌሎች ማካፈል ትወድ ነበር።

​

አቢጋይል ከወላጆቿና ከጓደኞቿ ጋር ስለ መጻሕፍት መወያየት፣ የወደደችውን ታሪክ ማስረዳት እና ያገኘችውን ትምህርት ማካፈል ትወድ ነበር።

​​​

አቢጋይል የራሷን ጽሑፎች ትጽፍ ነበር። ሀሳቦቿን፣ ስሜቶቿን እና የፈጠራ ችሎታዋን በጽሑፍ ማሳየት ትወድ ነበር።

​

ከምትወዳቸው ደራሲዎች መካከል Toni Morrison አንዷ ነበረች። አቢጋይል ጥልቅ ትርጉም ያላቸው ታሪኮችን እና የሰዎችን ሕይወትና ስሜት በቃላት የማሳየት ችሎታን ታደንቅ ነበር።

እንዲሁም ግጥምን በጣም ትወድ ነበር። ግጥም ስሜትን፣ ምናብን እና የቃላትን ውበት ለመግለጽ መንገድ ነበር ብላ ታምናለች።

​

​የአቢጋኤል የመጽሐፍ ማዕድ

ወደ አቢጋኤል የመጽሐፍ ማዕድ እንኳን በደህና መጡ።

ይህ ቦታ የንባብ፣ የታሪክ እና የፈጠራ ፍቅርን ለማካፈል የተዘጋጀ ነው።

​

እርስዎም፦

  •  የሚወዱትን መጽሐፍ ግምገማ ማጋራት ይችላሉ

  •  አጭር ታሪክ ወይም ግጥም መጻፍ ይችላሉ

  •  ከመጽሐፍ ያገኙትን ትምህርት ማካፈል ይችላሉ

  •  ያነበቡትነ መጽሀፍ  መጠቆም ይችላሉ

  • ለአቢጋይል መታሰቢያ ጽሑፍዎን ማካፈል ይችላሉ 

​

የፋውንዴሽኑ ዋና አላማዎች፡

  • የአቢጋኤል ዮሐንስ ፋውንዴሽን (Abigail Yohannes Foundation) ሦስቱ ዋና ዋና መሠረታዊ ምሰሶዎች (3 Pillars)፦

  • ፩. የአእምሮ ጤና ግንዛቤና ድጋፍ (Mental Health Awareness)

  •  ለወጣቶችና ለቤተሰቦች ጤናማና አጋዥ የሆኑ ከባቢዎችን መፍጠር፣ ግንዛቤን ማሳደግ እንዲሁም ተገቢውን የስነ-ልቦና ድጋፍና ግብአቶችን ማመቻቸት።

  • ፪. የንባብና የመጻሕፍት ባህልን ማሳደግ (Literacy & Reading)

  •  መጻሕፍትን ለአካባቢ ቤተ-መጻሕፍት ማበርከት እንዲሁም በአቢጋኤል መታሰቢያ የተሰየሙ ልዩ የንባብ መደርደሪያዎችን (“Abigail’s Shelf”) በማቋቋም ንባብን ለሁሉም ተደራሽ ማድረግ።

  • ፫. የማኅበረሰብ ቤተ-መጻሕፍት ግንባታ (Community Library in Ethiopia)

  •  የረጅም ጊዜ ራዕይ የሆነውን የማኅበረሰብ ቤተ-መጻሕፍት በኢትዮጵያ ውስጥ በመገንባት ለትውልድ የሚተላለፍ የዕውቀትና የትምህርት ማዕከል መመሥረት።

IMG_2344.jpeg
Screenshot 2026-09-20 210338.png
Screenshot 2026-09-20 210412.png

Abigail Yohannes Foundation Corp is a registered 501(c)(3) tax-exempt nonprofit organization. EIN: 42-3606109

bottom of page